ማሊ ውስጥ ከአይቮሪ ኮስት የሽብር ጥቃት ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለሥልጣት አስታወቁ

ፖሊስ ወደ ግራንድ ባሳም አይቮሪ ኮስት እያመሩ እ.አ.አ. 2016

​​ሌሎች 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደሚገኙም፣ የአካባቢው ዐቃብያነ -ህግ አስታውቀዋል።

ማሊ ውስጥ ባለፈው ወር ቢያንስ 19 ሰዎች ከተገደሉበት የሽብር ጥቃት ጋር በተያያዘ ከአል-ቃዒዳ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለሥልጣት አስታወቁ።

የፖሊስ መግለጫ እንዳመለከተው ሰዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፉት 48 ሰዓታት ሰሜናዊ ማሊ ውስጥ ሲሆን ይህም፣ ግራንድ ባሳም (Grand-Bassam) በተባለው የአይቮሪ-ኮስቱ መዝናኛ ስፍራ በሚገኙ ሦስት ሆቴሎች ውስጥ የደረሰው ጥቃት በተካሄደ በ3ኛው ወር መሆኑ ነው።

ለሽብርተኞቹ እንደ ሾፌር ሆኖ ወደ አይቮሪ-ኮስት ያመጣቸው ኦልድ መሐመድ (Ould Mohamed) የተባለው ከተጠርጣሪዎቹ አንደኛው ሲሆን፣ የጥቃቱ ዋነኛ አቀነባባሪ መሆኑንም፣ የፈረንሳይ ዜና አውታር ዘግቧል።

ሌሎች 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደሚገኙም፣ የአካባቢው ዐቃብያነ -ህግ አስታውቀዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ታጣቂዎች በአይቮሪ ኮስት ግራንድ ባሳም መዝናኛ ስፍራ ላይ ዛሬ ጥቃት ፈጽመዋል