ሁለት ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ

ዶ/ር አበበ ሃረገውይንና አብርሃም ተፈሪ ዲሲ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP)ጽ/ቤት ከ30,000 ዶላር በላይ የሰበሰቡትን ገንዘብ ሲያስረክቡ

ሁለት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ከ30,000 ዶላር በላይ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ ሰብስበው በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል።

ጎ-ፈንድ-ሚ ወይም (GoFundMe) በግርዱ ወደ አማርኛ ሲመለስ፤ “ድጋፍህን ስጠኝ፤” በሚል ስያሜ በሚታወቀውና በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከ1 ቢልዮን ዶላር በላይ በ 365 ቀናት ውስጥ ሊሰበስቡ የሚችሉበት ድረ-ገጽ ነው።

ሁለት ኢትዮጵያውያን፣ ዶ/ር አበበ ሃረገውይንአብርሃም ተፈሪ ድረ-ገጹን በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ አሰባስበዋል። እስከ ዛሬ ከ30,000 ዶላር በላይ የሰበሰቡ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል።

ሳሌም ሰለሞን በርክክቡ ላይ ተገኝታ ያጠናቀረችውን ቃለ-ምልልስ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሁለት ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ

በተጨማሪም የቪድዮ ፋይሉን በመጫን የኢትዮጵያኑን መልእክት ይመልከቱ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሁለት በዳያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ

የፎቶ መድብሎቻችንንም ከዚህ በታች ካለው ፋይል ይመልከቱ።

ሁለት ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ