የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ገዢ ፓርቲን ወክለው እንደገና ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ ዛሬ አስታውቀዋል

  • ቪኦኤ ዜና

የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሕመት ዳቩቶግሉ

የፍትህና የልማት ፓርቲ የተባለው ገዢ ድርጅት ከፍተኛ ኮሚቴ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንካራ በተደረገ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ ለፓርቲው አንድነት ሲባል የሊቀመንበር ለውጥ ማደረግ ተገቢ ነው ብለዋል።

የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሕመት ዳቩቶግሉ የሀገሪቱን ገዢ ፓርቲ ወክለው እንደገና ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ ዛሬ አስታውቀዋል።

የፍትህና የልማት ፓርቲ የተባለው ገዢ ድርጅት ከፍተኛ ኮሚቴ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንካራ በተደረገ ጋዜጣዊ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ ለፓርቲው አንድነት ሲባል የሊቀመንበር ለውጥ ማደረግ ተገቢ ነው ብለዋል።

“ይህን ውሳኔ በማድረጌ የሚሰማኝ ጸጸትም ሆነ የውድቀት ስሜት የለኝም። ስንብቱ እኔ ፈልጌው ሳይሆን አስፋላጊ በመሆኑ ነው” ብለዋል። ለውሳኔው ባስገደዳቸው ሁኔት ላይ የሚሰማቸው ምሬት እንደሌልም በአጽንኦት አስገንዝበዋል።

የቱርክ ፕረዚደንት ታይብ ኤርዶጋን ከቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሕመት ዳቩቶግሉ ጋር እ.አ.አ. 2015

ዳቩቶግሉ አያይዘውም የገዢው ፓርቲ የምክር ቤት አባል በመሆን ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል። ለቱርክ ፕረዚዳንት ሪሴፕ ታይፕ ኤርዶጋን ታማኝነታቸውን ገልጸዋል። ውሳኔው የራሳቸው እንደሆነ አስገንዝበው ለረዚዳንቱ በጎውን ተመኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁኑኑ ከስልጣን ተሰናብተዋል ማለት አይደለም። ገዢው ፓርቲ እ.አ.አ. ግንቦት 22 ላይ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቩቶግሉን የሚታካ አዲስ መሪ ይመርጣል።