የኦሮሚያ ክልል ፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንዳዓ ታሰሩ

የኦሮሚያ ክልል ፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንዳዓ

"ለፍተሻ ሲያመጡት እጆቹን በካቴና ታስሮ ነበር” - ባለቤታቸው "አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሰዎችን ዝም ማሰኛና ትችንት ወንጀል ማድረጊያ መሳሪያ ነው”- አምነስቲ

የኦሮሚያ ክልል ፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንዳዓ በዛሬው ዕለት መታሰራቸውን ባለቤታቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። አቶ ታዬ ቅዳሜ መጋቢት 1/2010 ዓ.ም የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሞያሌ ከተማ ዐሥር ሰዎች መግደላቸውና ዐሥራ አንድ ሰዎች ማቁሰላቸው “በስሕተት የተፈፀመ ነው” ብሎ ቢሮአቸው እንደማያምን ለአሜሪካ ድምፅ መግለፃቸው ይታወሳል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሰዎችን ዝም ማሰኛና ትችንት ወንጀል ማድረጊያ መሳሪያ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል ከግድያው በኋላ ሸሽተው ወደ ሞያሌ ኬንያ የተሰደዱንት ኢትዮጵያውያን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ መቀጠሉን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሚያ ክልል ፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንዳዓ ታሰሩ