ዋሽንግተን ዲሲ —
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ፤ ጉዳዩን ዓለም ሊያውግዘው የሚገባ በአካባቢው እንደተባለው ኦነግ ቢኖር እንኳን ከማሰር የዘለለ እርምጃ ሊወሰድ አይገባም ነበር ብሎታል።
ከመስከረም ወር ወዲህ ብቻ እንኳን ተደጋጋሚ የጅምላ ግድያዎች እየተፈፀመ ነውም ብሏል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ ቀደም የሚነሱትንም ሆነ የአሁኑን በተመለከተ ሪፖርት አጠናቅሮ ዝግጁ ማድረጉን ገልፆ ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች በመሆኑ ለማቅረብ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ “ሸዋበር” በተባለ የመኖሪያ መንደር በትናንትናው ዕለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፈፀሙት ጥቃት ዐሥር ሰዎች ተገድለው ሌሎች ዐሥራ አንድ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች፣ የከተማው አስተዳደርና ኮማንድ ፖስቱ አረጋግጠዋል። ይህን በተመለከተ የቀደመውን ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ