ዋሽንግተን ዲሲ —
ቅዳሜ ዕለት ከኢትዮጵያ ሞያሌ ወደ ኬንያ ሞያሌ የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቁጥር እየወጣ ሲሆን ስደተኞቹ ባሉበት ቦታ ተገኝቶ እየሠራ ያለው የኬንያ ቀይ መስቀል አሁንም ስደተኞቹን በመመዝገብና በመቁጠር ላይ በመሆኑ ቁጥሩ እያሻቀበ መሆኑን ተናግሯል።
ሸሽተው ድንበሩን ከተሻገሩ ኢትዮጵያውያን መካከል በአሁኑ ወቅት በአምስት ቦታ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀው ቀይመስቀል ለሴቶችና ለሕፃናት ቅድሚያ በመስጠት እየመዘገበ እንደሆነ ተናግረዋል። በትናንትናው ምሽት ሜዳ ላይ በዝናብ ሲበሰብሱ ማደራቸውንም ገልፀውልናል።
በሌላ በኩል በሞያሌ ከተማ ዘመድ የሞተባቸውና የቆሰሉ ሰዎችን አነጋግረን ሰዎች ሁሉ ሸሽተው ከተማው ባዶ መሆኑን ነግረውናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ