በዛሬው ዝግጅት የማሕበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን በኦሮሚያ የተቃውሞ ሰልፎች ያለውን ሚና እንገመግማለን። እነዚህን ሁኔታዎች በማሕበረሰብ ድረገጽ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለውና ከ435 ሽህ በላይ ተከታዮች ያሉት ጃዋር ሲራጅ መሀመድ ጋር ከተደረገው ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በህዳር ወር የመጀመሪያ ሳምንት፤ በኦሮሚያ ጊንጪ ከተማ አካባቢ የሚገኝ ደን ለአንድ የግል ኢንቨስተር መሸጡና የአንድ ትምህርት ቤት እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳም እንዲሁ “ለልማት” በሚል ተሰጠ ሲሉ የከተማዋ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጡ።
የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃንም በዚያን ቀን #OromoProtests በሚል በብዛት በፌስቡክና በትዊተር መልእክቶች፣ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት መሰራጨት ጀመሩ።
በማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ከሚሰራጩት መልእክቶች፤ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች መካከል የሚበዙት ከዩናይትድ ስቴይትስና ከአውሮፓ የወጡ ናቸው፤ የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እንቅስቃሴን የሚከታተለው “Keyhole Hashtag Tracking” መረጃ መሰረት።
41 ከመቶ ከዩናይትድ ስቴይትስ፤ 9ከመቶ ከካናዳ፤ ከአውሮፓ ደግሞ ወደ 25 ከመቶ የሚጠጋ፤ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ 17 ከመቶ መረጃዎች መጥተዋል።
በዛሬው ዝግጅት የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን በኦሮሚያ የተቃውሞ ሰልፎች ያለውን ሚና እንገመግማለን።
እነዚህን ሁኔታዎች በማህበረሰብ ድረገጽ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለውና ከ435 ሽህ በላይ ተከታዮች ያሉት ጃዋር ሲራጅ መሀመድ ጋር ከተደረገው ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5