በፓሪስ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ ተገድሏል

  • ሰሎሞን ክፍሌ
በቻርሊ ሄብዶ (Charlie Hebdo) መጽሔት ማደራጃ ቢሮ ላይ የደረሰው ጥቃት የመጀመሪያ ዓመት በሚታሰብበት እለት በፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ ተገድሏል።

ዛሬ ፓሪስ ውስጥ፥ ጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን በቻርሊ ሄብዶ (Charlie Hebdo) መጽሔት ማደራጃ ቢሮ ላይ ያደረሰው ጥቃት የመጀመሪያ ዓመት በሚታሰብበት እለት፥ አንድ በፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ ተገድሏል።

አንድ የፈረንሳይ ሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ባለሥልጣን ስለዚሁ ሲናገሩ፥ ስለት የያዘው ግለሰብ፥ ወደ ፖሊስ ጣቢያው በቀረበበት ወቅት ፈንጅ የታጠቀ ይመስል ነበር ብለዋል።

ግለሰቡ በፖሊስ ተተኩሶበት ከመሞቱ በፊት፥ “አላሁ አክበር” ወይም “እግዚአብሔር ታላቅ ነው” እያለ ሳይጮህ አልቀረም ሲሉም የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴሩ ባለሥልጣን አስረድተዋል።

ድንገቱ እየተጣራ መሆኑም ተዘግቧል።

ፕሬዘዳንት ፍራንሷ ሆላንድ (Francois Hollande)ፖሊሶችን ሰላም እያሉ

ፕሬዘዳንት ፍራንሷ ሆላንድ (Francois Hollande)ፖሊሶችን ሰላም እያሉ

በሌላ ዜና፥ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ፍራንሷ ሆላንድ (Francois Hollande) የሄብዶ (Hebdo) ቢሮ በተጠቃበት ወቅት፥ የዜጎችን ሕይወት ሲከላከሉ የሞቱት ሦስት ፖሊሶች በታሰቡበት ሥነ-ሥርሣት ላይ፥ ለታጣቂ የፖሊስ መኮንኖች አዲስ የፀጥታ ጥበቃ መመሪያ አስተዋውቀዋል።

ፖሊሶች ከሥራ ውጪም ትጥቃቸውን መያዝ ይችላሉ፥ 5 ሺህ ተጨማሪ ፖሊሶችም ይመደባሉ ብለዋል።

ባሁኑ ወቅት በየትምህርት ቤቱ ደጃፍ፥ በአውሮፕላን ማረፊያዎችና በሌሎች ሕዝብ በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች፥ የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል የተመደቡትን የፀጥታ ጠባቂዎች አመስግነዋል።

የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

Your browser doesn’t support HTML5

በፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ ተገድሏል