በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ፍራንሷ ኦላንድ ከአቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል


ፕሬዚደንት ኦላንድ ከዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል።

በእስላማዊ አማጽያን ላይ ዘመቻው እንዲጠናከር ጥሪ የሚያደርጉትና ትብብርም የሚሹት የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ፍራንሷ ኦላንድ ዛሬ ማክሰኞ ወዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ማምራታቸው ተገለጸ። እናም ፕሬዚደንት ኦላንድ፣ ከዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል።

የፈረንሳዩ መሪ ኦላንድ፣ ይህንኑ የትብብር ጥሪ በመያዝ ትናንት ሰኞ ከብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቢድ ካሜሩን ጋራ የተወያዩ ሲሆን፣ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ገደማ ደግሞ ከሩስያ፣ ከቻይና፣ ከጀርመን እና ከኢጣልያ መሪዎች ጋራ እንደሚገናኙ ተገልጧል።

ኋይት ሀውስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፣ ኦባማና ኦላንድ በተጨማሪ የትብብር ስምምነት ላይም ይወያያሉ። ይህም ውይይት፣ ሦርያና ኢራቅ ውስጥ በሚገኙ የእስላማዊው መንግሥት ስትራተጂካዊ ዒላማዎች ላይ የሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ መራሹ የአየር ጥቃት አካል መሆኑንም አመልክቷል።

ፈረንሳይ ሰፊና የተጠናከረ የአየር ጥቃት ለማካሄድ ያወጣችውን ዕቅድ ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትደግፈው የኋይት ሀውሱ ቃል-አቀባዩ ጆሽ እርነስት (Josh Earnest) አመልክተዋል። ዛሬ አጭር ዜና ይዘን ቀርበን ነበር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ፕሬዚደንት ኦላንድ ከዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:41 0:00

የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ፍራንሷ ኦላንድ ከአቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00

XS
SM
MD
LG