በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓሪስ ኢትዮጵያዊያን በጥቃቱ ሰዓት የት ነበሩ? ምን ተሰማቸው?


አይፈል ታወር (The Eiffel Tower)
አይፈል ታወር (The Eiffel Tower)

ፓሪስ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለፈው ዓርብ የሽብር ጥቃቶች ከተካሄዱባቸው አካባቢዎች በየትኛውም ሥፍራ መቼም ሊገኙ ይችሉ እንደነበር እዚያው የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ገልፀውልናል፡፡

የሽብር ድርጅቶችና መረቦች ተፈጥሮና የእንቅስቃሴዎቻቸው ዓይነት ለሚያደርሷቸው ጥቃቶች የተመቸ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው በሽብርና በዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ላይ የሚሠሩት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልክያስ ለቪኦኤ በሰጡት ትንተና አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ሽብተኞች እንቅስቃሴዎቻቸውን ከኢራቅና ከሦሪያ ውጭ የሚያስፋፋበትን አዲስ ስልት እያወጡ ናቸው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የስለላ ኤጀንሲ - ሲአይኤ ዳይሬክተር ጃን ብሬናን ዛሬ አስታውቀዋል፡፡

“የአይሲል የግድያ መስኮች ከእንግዲህ ኢራቅና ሦሪያ ብቻ አይደሉም” ብለዋል ብሬናል ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ዓለም አቀፍና ሥልታዊ ጥናቶች ተቋም ውስጥ ሲናገሩ፡፡

“አይሲል ለግድያ የሚጠቀምበትን የውጭ አጀንዳውን ተግባራዊ እያደረገ ነው፤ በአይሲል የተደቀነው ክስተት ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንዲተባበርና ጥረቱን እንዲያቀናጅ ያስገድዳል” ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ብሬናን አክለውም እንዲህ ዓይነቱ የተጠናከረ ትብብር መኖር ያለበት በመረጃ ልውውጥ፣ በጋራ በሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች፣ በሕግ አፈፃፀም፣ በወታደራዊ ዘመቻዎች፣ በዲፕሎማሲ መስኮች መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በአይሲል የተደቀነውን ሥጋት አጣጥላ እንደማታየው የሲአይኤው ዳይሬክተር ጃን ብሬናን ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓሪስ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለፈው ዓርብ የሽብር ጥቃቶች ከተካሄዱባቸው አካባቢዎች በየትኛውም ሥፍራ መቼም ሊገኙ ይችሉ እንደነበር እዚያው የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ገልፀውልናል፡፡

ለሙሉው ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የፓሪስ ኢትዮጵያዊያን በጥቃቱ ሰዓት የት ነበሩ? ምን ተሰማቸው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:26 0:00

XS
SM
MD
LG