በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ መምሕራንና ተማሪዎች ታሥረው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን እንዲሁም ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን በከተማው ውስጥ የሚገኝ የገበያ ቦታ መቃጠሉን በዚህ ቃጠሎም የመንግሥት እጅ አለበት የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አቶ ኩመላ ኬና የተባሉ የመንዲ ከተማ ነዋሪ ስለ ሁኔታው ሲናገሩ፤ ሰኞ መጋቢት12 ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ የሚወስደው መንገድ አምስት ቦታ ዘግተዋል ያሏቸውን ሰዎችለመያዝ የከተማውና የፌደራል ፖሊሶች ከተማ ውስጥ ገብተው፤ ዐሥራ ሰባት መምሕራንናተማሪዎችን አሥረው ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዳቸውን፣ እንዲሁም ማክሰኞ መጋቢት 13ቀን በከተማው ውስጥ የሚገኝ የገበያ ቦታ መቃጠሉን፣ በዚህ ቃጠሎም የመንግሥት እጅአለበት የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ይህን በተመለከት የአካባቢው ፖሊስ ምንም የማውቀው ነገር የለም ሲል የከተማው ከንቲባበበኩላቸው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ሰዎች እንደተለቀቁ ገለፀዋል።
የገበያ ቦታውመቃጠሉን አምነውም ማጣራት እየተደረገ ነው ብለዋል።
የኦሮመኛ ዝግጅት ከፍል ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማታቀርበዋለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5