በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል

በኦሮምያ ክልል በህርና የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ (ከማኅበራዊ ሚድያ የተገኘ ፎቶ)

በሳምንቱ ማብቂያ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዛሬ ተቃውሞ እንደተካሄደባቸው ከተገለጹት መካከል፥ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሜሦ ወረዳና ምዕራብ ሸዋ ይገኙበታል።

ኡርፎና ሶዶም በምትባል ከሜሦ 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፥ የሶማሌ ክልል ሰዎች ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በአርሦ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍተው ስድስት ሰዎችን ገድለዋል።

አንድ የከተማዋ ነዋሪ ሲናገሩ ግን፥ ከተኳሾቹ መካከል አንደኛው የመንግሥት ወታደር መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል። በሁኔታው ሕዝቡ በጣም ተቆጥቶ ተቃውሞውን ለመግለጽም፥ ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የሚሄደውን መንገድ ጎማና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማቃጠል ዘግቷል ሲሉም፥ እኚሁ የከተማዋ ነዋሪ ጨምረው ገልጸዋል።

የሚኤሦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ጀማል በሰጡት መልስ። ”የሞቱ ሰዎች አሉ። የሞቱት ግን ባካባቢው በሚኖሩ አርብቶ አደሮች በሱማሌና ኦሮሞ መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ነው።

መከላከያ ሠራዊቱ በዚያ የተገኘውም ሁለቱን ማህበረሰቦች ለማስታረቅ እንጂ በግድያው አልተሳተፈም” ብለዋል። ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል