የትላንት በስቲያው የሚኤሶ የተቃውሞ ሰልፍ

በኦሮምያ ክልል በሃረርጌ ዞን ሂርና ከተማ የተቃውሞ ሰልፈኞች(ከማኅበራዊ ሚድያ የተገኘ ፎቶ) Hiriira Mormii Oromiyaa

“ካራ በተባለ ሥፍራ ነው፤ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ላይ ፖሊስ ተኩሶ የገደለው። በቀደመው ሰልፍ ላይ በመሳተፉ ነው፤ የተገደለው።” አንድ የሚኤሶ ከተማ ነዋሪ። “በመጀመሪያ ልዩ ፖሊስ ኃይል የሚባል በወረዳችንም ሆነ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የለም። ይህ ፕሮፖጋንዳና የሃሰት ወሬ ነው። በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሥርዓት መሠረት ሰው በሰላም የመኖር መብት አለው።” አቶ መሃመድ ጀማል የሚኤሶ ወረዳ ምክትል ሊቀ መንበር።

ከሁለት ወራት በላይ ያስቆጠረው በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎችና አንዳንድ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የአዲስ አበባንና የፊንፊኔ ሪያ ዞኖች የማስተር ፕላን (የከተማ ማስፋፊያ) እቅድ አስመልክቶ የተቀሰሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።

በሃረርጌ ዞን ከተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የሁለት ወጣቶች ሕይወት መጥፋቱን አንዳንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የአካባቢው ባለ ሥልጣናት ግን የተባለውን ውንጀላ ያስተባብላሉ።

በርዕሱ ላይ የተጠናከሩትን ዘገባዎች ከዚህ ያድምጡ፤

Your browser doesn’t support HTML5

የትላንት በስቲያው የሚኤሶ የተቃውሞ ሰልፍ