የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የድርጅቱ አመራር አባላት በጠቅላላው ሃያ ሁለት ተከሣሾች ዛሬ በተያዘላቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሳይቀርቡ ቀርተዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የድርጅቱ አመራር አባላት በጠቅላላው ሃያ ሁለት ተከሣሾች ዛሬ በተያዘላቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሳይቀርቡ ቀርተዋል።
ተከሣሾቹ እሥር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
ላለመቅረባቸው ምክንያቱ ምን እንደሆነ የተጠየቀው የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የሰጠው መልስ የለም።
አዲስ አበባ የሚገኘውን ዘጋቢያችንን መለስካቸው አምሃን ያነጋገሩ ምንጮች እንደሚሉት ግን ለተከሣሾቹ አለመቅረብ ምክንያት የሆነው የልብሳቸው ቀለም ነው።
ፍርድ ቤቱ በዚሁ በዛሬው ውሎው የተለያዩ ትዕዛዞችን ሰጥቷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5