ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ ሕዝባዊ ስብሰባ በቅርቡ ጎንደር ከተማውስጥ ተካሂዷል።
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ተጠቃልሎ የሚገኘው የወልቃይት አካባቢ ሰዎች ተወካዮቻቸውን ሰይመውና የሃምሣ ሺህ ሰው ፊርማ አሰባስበው መካለል ያለብን ወደ ትግራይ ሳይሆን ወደ አማራ ነው ብለው ጥያቄአቸውን ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ልከው እንደነበር ተዘግቧል።
በሌላ በኩል ደግሞ የተባለው የወልቃይት የማንነት ጥያቄ “የሌለ፣ የሻዕቢያና ግንቦት ሰባት አርበኞችን የመሳሰሉ አካላት ሴራ ነው፤ ልማትን ለማደናቀፍ የሚደረግ ፀረ-ሰላም እንቅስቃሴ ነው” ሲሉ ሁመራ ተሰብስበው የነበሩ ከአራቱም ወረዳዎች የተውጣጡ ናቸው የተባሉ ስድስት መቶ ተሣታፊዎች የተገኙበት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ የመሩት ስብሰባ ጥያቄውን አውግዞና የአቋም መግለጫ አውጥቶ መበተኑ ይታወሣል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን ጎንደር ላይ የተጠራው ስብሰባ የወልቃይትን ኮሚቴ ጠርቶ ማብራሪያ መጠየቁንና ውይይት ማካሄዱን፤ በኮሚቴው አባላትና በተሰብሳቢው መካከል ጥያቄና መልስ እንደነበረ፤ ከሃገር ሽማግሌዎቹ አንዱ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የጎንደር ባለሥልጣናትን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግናቸው ጥረቶች አልተሣኩም።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5