ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል 121 ተጨማሪ እስረኞች ተከሰሱ

ቅዳሜ ነሐሴ 28 ቀን 2008 በቂልንጦ ማረሚያ ቤት የደረሰው የእሳት ቃጠሎ

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል 121 ተጨማሪ እስረኞች ተከሰሱ። ተከሳሾቹ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ከሳቸው እየተነበበላቸው ይገኛል። በዛሬው ዕለትም ቀኑን ሙሉ ክስ የመስማት ሂደት ተከናውኗል። በክስ መስማቱ ሂደት ተከሳሾቹ ባሰሙት አቤቱታ በችሎቱ መረባበሽ ነበር ተብሏል።

ከአምስት ወራት በፊት ቅዳሜ ነሐሴ 28 ቀን 2008 በቂልንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 23 ሰዎች መሞታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም በዚህ የቃጠሎ አደጋ በማድረስ ተጠርጥረው ክስ ከመሰረተባቸው 38 እስረኞች በተጨማሪ ሌሎች 121 እስረኞች ተከሰው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ተከሳሾቹ የቀረብባቸው የክስ ዝርዝር ውስጥ እስረኞችን እሳት ውስጥ ወርውሮ በመጨመር እና በፌሮ ብረት መቶ መግደል ይገኝበታል።

በክስ መስማቱ ሂደት አብዛኞቹ ተከሳሾች በጠበቃ ይወከሉ እንደሆነ ሲጠየቁ ፤ የእግዚያብሔር እና የመላዕክትን ስም በመጥራት ጠበቆቻቸው እነርሱ እንደሆኑ ሲገልጹ ነበር ተብሏል። ለዳኞች እንደተነሱ በቆሙበት የሕሊና ፀሎት አድርገዋል ተብሏል።

ጽዮን ግርማ ከተከሳሾቹ ውስጥ የሁለቱን ጠበቃ እና አንድ ቤተሰብ አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

Your browser doesn’t support HTML5

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል 121 ተጨማሪ እስረኞች ተከሰሱ