የሲድስ ኦፋ አፍሪካ (Seeds of Africa) መስራች አትጠገብ ወርቁ (አቲ ወርቁ) እ.አ.አ በ2005 የኢትዮጵያ ሚስ ዩኒቨርስ የቁንጅና ውድድር ላይ አሸናፊ ነበረች። በናዝሬት ከተማ በኑሮ አነስተኛ ለሆኑ ህፃናትና ወጣት ነዋሪዎች ትምህርት ቤት ለመክፈት ይውል ዘንድ ከ1.3 ሚልየን ዶላር በላይ በማሰባሰብ እቅዷን ያሳካች ወጣት ናት።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በአዳማ- ናዝሬት ፤ ተወልዳ ባደገችበት ሰፈር አራዳ፤ በአብሮአደጎቿ ላይ የነበረው የኑሮ ጫና በተለይም በክፍያ እጦት ምክንያት እኩዮቿ ትምህርታቸውን ከዳር ያለማድረሳቸው ያሳስባት ነበር። የበኩሌን ምን ማድረግ አለብኝ ብላ ራሷን መጠየቅ የጀመረችውም በደቡብ አፍሪካ በነበራት ቆይታዋ ደቡብ አፍሪካውያኑ እርስ በርስ አንዴት ችግራቸውን እንደሚፈቱ ከተመለከተች በኃላ ነበር።
በአትጠገብ ወርቁ የተመሰረተው "Seeds of Africa" ከ1.3 ሚልዮን ዶላር በላይ አሰባስቧል። “በአብዛኛው ገንዘብ በቃል የተገባልን ቢሆንም በቅርቡ በእጃችን እንደሚገባና ያሰብነውን ከዳር አንደምናደርስ አርግጠኛ ነኝ” ትላለች አቲ።
አትጠገብ (አቲ) ወርቁ “AYE” የአፍሪካ ምርጥ ወጣት ሽልማት፤ ከተሰኘው የሽልማት ድርጅት ባለፈው አመት ለሀገሯ ባደረገችው ታላቅ ስራ ተሸላሚ ሆናለች። AYE “The African Youth Excellence Awards” ከሀገራቸው ውጭ በተለይም በአሜሪካ የሚኖሩ ወጣት አፍሪካውያንን ለትውልድ ሀገራቸው ለሚሰሩት በጎ ምግባርን ለማባረታታት ሽልማትን በመስጠት ይታወቃል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ!
Your browser doesn’t support HTML5