"ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ያላቸውን ቅሬታ በዚህ አግባብ ቢገልጹ ምንም ክፋት የለውም"የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
አድማው ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል
በኦሮሚያ ክልል የቀን ገቢ ግምት መጨመር ጋር በተያያዘ የተነሳው ሥራ የማቆም አድማ ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በትናንትናው ዕለት በአምቦና በወሊሶ ከተማ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች፤ አድማው በዛሬው ዕለትም መቀጠሉን ይናገራሉ። በወሊሶና በአምቦ ከተማ ዛሬም የንግድ ቤቶች ተዘግተው ትራንስፖርትም ተቋርጦ መዋሉን ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አምቦ፣ወሊሶ፣ ጊንጪና ደንቢ ዶሎ አካባቢ አድማ መኖሩን አረጋግጠው ሌሎች አካባቢዎች ግን በሰላማዊ መንገድ ሂደቱ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።