“በርካታ ተማሪዎች እሥር ቤት ታጉረዋል” የነጆ ከተማ ነዋሪ

የኦሮሚያ ክልል ካርታ /ምንጭ - ተመድ/

በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ እስካሁን በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ውጥረት መንገሱን፣ የመማር ማስተማር ሂደቱ መስተጓጎሉንና ተማሪዎች ከሚማሩበት ትምሕርት ቤት እየታሠሩ እንደሚወሰዱ አንድ የነጆ ከተማ ነዋሪ ተናገሩ፡፡ ፖሊስ ከተማዋ ሠላም መኾኗን ይናገራል፡፡ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ከሠላሣ ተማሪዎች በላይ ታሥረው እንደሚገኙና ከእንዚህም መካከል ሁለቱ ባለፈው ቅዳሜ ፍርድ ቤት ቀርበው ሕዝብን ለተቃውሞ ማነሳሳት በሚል ክስ ሁለት ወር እስር እንደተፈረደባቸው አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የነጆ ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል፡፡

ከተማው በውጥረት መኾኑን የገለጹት እኚህ ነዋሪ “በአሁኑ ሰዓት በርካታ ተማሪዎች እሥር ቤት ታጉረዋል፡፡ ገሚሶቹ ከከተማ የቀሩት ደግሞ ከትምሕርት ቤት የተያዙ ናቸው፡፡የሚታሠሩትም ተማሪውና ሕዝቡ ጥያቄ እንዲያነሳ ቀስቅሳችኋል በሚል ነው”ይላሉ፡፡

የነጆ መሰናዶ ትምሕርት ትምሕርት ቤቱ ርእሰ መምሕር በበኩላቸው ትምሕርት በዚህ ሣምንት መጀመሩን ገልጸው፤ “ተማሪዎች ከትምሕርት ቤት ሲለቀቁ መንገድ ላይ ይጮሃሉ፡፡ በዚህን ጊዜ የጸጥታ ኃይሎች ይይዟቸዋል እንጂ ከትምሕርት ቤት አይታሠሩም፡፡’’ ብለዋል፡፡

ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

“በርካታ ተማሪዎች እሥር ቤት ታጉረዋል” የነጆ ከተማ ነዋሪ