ላለፉት አስራ አራት ዓመታት ኤርትራ ዉስጥ ታስሮ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት የፔን ኢንተርናሽናል ተሸላሚ ሆኗል። ባለፈዉ ጥር ስድስት ሄግ ዉስጥ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ለመናገር መብት ከታገሉ አንዱ በመባል ከግብጽ ከቱርክና ጋዜጠኞች ጋር የዓመቱ የፔን ተሸላሚ ሆኗል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የታገደዉ ዘመን የተባለዉ የኤርትራ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረዉ አማኑኤልአስራት እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከእአአ 2001 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በአገሪቱ እስር ቤትዉስጥ ነዉ የሚገኘዉ።
ሄግ ዉስጥ የሚገኘዉ Writers Unlimited Interantaoal የተባለዉ ከጋዜጠኞች መብት አስከባሪ ድርጅት Pen International ጋር በመተባበርየሚሰራዉ ዓለም አቀፍ ድርጅት ባዘጋጀዉ ስነስርዓት ከዓመቱ የፔን ተሸላሚዎች አንዱሆኖአል።
በፔን ኢንተርናሽናል (Freedom to Write) የተባለዉ ፕሮግራም ዳይሬክተር አን ሃሪሰን(Ann Harrison) ለዜጠኛ አማኑኤል አስራት የዓለም አቀፉ ድርጅት ሽልማት የሰጠበትን ምክንያት ሲገልጹ ኤርትራ ዉስጥ ያለዉ የመናገርና የመጻፍ መብት እጅግ አሳሳቢ ሆኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ጋዜጠኛዉ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ከአስራ አራት ዓመት በፊት የተሰወረ መሆኑን ጠቅሰዉ ይሙት ይኑር ባይታወቅም ለእርሱ ይህን ሽልማት በመስጠት በአገሪቱ ዉስጥ ምንም የመናገር የመጻፍ መብት እንደሌለ ልናሰምርበት ነዉ ብለዋል።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን ሙሉዉን ዘገባ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5