የኮንጎ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔውን የሰጠው ከገዢው ፓርቲ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መሆኑ ተገልጿል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የስልጣን ዘመናቸው እ.አ.አ. በዚሁ በ2016 ዓመተ ምህረት የሚያበቃው የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ ፕሪዚደንት ጆሴፍ ካቢላ ከዚያ በፊት ካልተካሄደ ስልጣን ላይ መቆየት ይችላሉ ሲል የሃገሪቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ።
የኮንጎ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔውን የሰጠው ከገዢው ፓርቲ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መሆኑ ተገልጿል።
የፕሬዚደንቱ የስልጣን ዘመን ማብቂያ እየተቃረበ ቢሆንም የሀገሪቱ መንግስት እስካሁን የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ አላወጣም። የአርባ አራት ዓመቱ ካቢላ እንደገና እንዳይወዳደሩ ህገ መንግስቱ ይከለክላል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፑብሊክ ህገ መንግስቱን የሚያከብር ተዓማኒ ምርጫ በወቅቱ እንድታካሄድ ባለፈው መጋቢት ወር ማሳሰባቸው አይዘነጋም።