በኢትዮጵያ የደረሰውን ድርቅ ለመቋቋምና ለማስወገድ፣ በድርቁም የሚጎዱ ወገኖችን ለመታደግ፣ ከአገር ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ዜጎች እርብርቦሽ እያደረጉ መሆናቸው ይታወቃል። ከዚህ አኳያ ዛሬ በምዕራብ ዳላስ ቴክሳስ የኢትዮጵያውያንን እንቅስቃሴ እንመለከታለን።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ የደረሰውን ድርቅ ለመቋቋምና ለማስወገድ፣ በድርቁም የሚጎዱ ወገኖችን ለመታደግ፣ ከአገር ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ዜጎች እርብርቦሽ እያደረጉ መሆናቸው ይታወቃል።
ለዚህ ዓላማ የተቋቋመውን ግብረ-ኃይል ያሰባሰበው፣ በዳላስ የኢትዮጵያውያን መረዳጃ ማኅበር ነው። ስለ መጪው እሑድ እ.አ.አ. ኤፕሪል 3 ቀን 2016 የገንዘብ አሰባሰብ ዝግጅትና መርሓ-ግብር አስተያየታችውን ለቪኦኤ የሰጡት ደግሞ፣ የመረዳጃ ማኅበሩ ዳይሬክረተር አቶ ብርሃን መኰንን እና የግብረ-ኋይሉ ቡድን የሕዝብ ግንኙነት ኋላፊ ወይዘሪት የትናየት ሳሙኤል ናቸው።
አቶ ብርሃን በሰጡት አስተያየት፣ ቢያንስ እስከ 200 ሰው እንደሚጠብቁና በትንሹ አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ለማሰባሰብ እንዳቀዱ ተናግረዋል።
የግብረ-ኃይሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ ወ/ት የትናየት በበሉላቸው፣ አብያተ-ክርስቲያናት፣ መስጂዶችና ሌሎችም ሕዝባዊ ተቋማት ለዚህ ዓላማ ታጥቀው እንደተነሱ፣ ይልቁንም ወጣቱ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን ፋይል በመጫን ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5