የኬንያ የምርጫ ኮምሽንና የተቃዋሚ ጥያቄዎች

“ብጥብጥና ቀውስ እንዲቀሰቀስ፥ አለያም ለገዛ ራስ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ከግጭት ቋፍ በሚያዳርሱ መንገዶችን አንገፋም፤ ነው ያሉት። እውነትና ፍትህ እንዲረጋገጥ እንሻለን። ለዚህም ነው የምርጫ ኮምሽኑ ሊቀመንበር ኃላፊነታቸውን በፍጥነት ለማስረከብ መዘጋጀት አለባቸው፤ የምንለው።” የተቃዋሚው መሪ Raila Odinga

በኬንያ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሥርዓት ላይ የሚደረግ የተሃድሶ ለውጥ በሁለቱ ጎራ ላሉትወገኖች መደራደሪያ ሊሆን እንደሚችል ተገለጠ።

ባለፈው ወር ተቃዋሚ ወገኖች የተጠሯቸው በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች በግጭት ቢጠናቀቁም፤በዛሬው ዕለት በተካሄደው የናይሮቢው ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተናገሩት የተቃዋሚው መሪ Raila Odinga ድርድሮች በሚካሄዱበት መንገድ ላይ ያተኮሩ ዕቅዶች በመነደፍ ላይ መሆናቸውንገልጠዋ።

የኬንያ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የዛሬውን የነጻነት ቀን ለማሰብ ናይሮቢ ላይ ሰላማዊ ሰልፍአካሂደዋል።

እውነትና ፍትህ እንዲረጋገጥ እንሻለን። ለዚህም ነው የምርጫ ኮምሽኑ ሊቀመንበር ኃላፊነታቸውን በፍጥነት ለማስረከብ መዘጋጀት አለባቸው፤ የምንለው።”
የተቃዋሚው መሪ Raila Odinga

በብዙ ሺህ ለተቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደረጉት የዋናው የተቃዋሚዎች ሕብረት፤በእንግሊዝኛው ምሕጻረ-ቃል CORD መሪ Raila Odinga በኬንያ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሥርዓትላይ ለሚደረግ የተሃድሶ ለውጥ ሁለቱ ወገኖች፤ (የኬንያ መንግስትና ተቃዋሚዎች) እስከ አርብ ባለውጊዜ አምስት-አምስት የፓርላማ አባላቶችን በየበኩላቸው ለመወከል መስማማታቸውን ይፋአድርገዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያን የምርጫ ኰሚሽን ለመቃወም ከተሰለፉ ሰዎች ቢያንስ 3 ተገድለዋል

ተቃዋሚዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ያለመቀየራቸውንና ዘጠኙ የምርጫ ኮምሽን አባላትም ከኃላፊነትእንዲወርዱ መጠየቃቸውን ኦዲንጋ አስረድተዋል።

Lenny Ruvaga ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል።

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ የምርጫ ኮምሽንና የተቃዋሚ ጥያቄዎች