የእንግሊዝ ንጉሥ ቻርልስ ሣልሳዊ የካንስር ህክምና መጀመራቸውን በኪንግሃም ቤተመንግሥት ዛሬ አስታወቀ።
ካንሰሩ መኖሩ የታወቀው በቅርቡ በተደረገላቸው ምርመራ መሆኑንም ቤተመንግሥቱ ገልጧል።
ይሁን እንጂ የካንሰር ሕክምናው በቅርብ ጊዜ ለደኅንነታቸው ሲባል ከተሰጣቸው የፕሮስቴት ዕጢ ሕክምና ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ዛሬ፤ ሰኞ የወጣው የቤተመንግሥቱ መግለጫ አስታውቋል።
የ75 ዓመቱ ንጉሥ ህክምናውን የጀመሩት ዛሬ ከመሆኑ በስተቀር ያለባቸው የካንሰር ዓይነት ምን እንደሆነ አልተገለፀም።
SEE ALSO: ቻርለስ ንጉሥ መሆናቸው በይፋ ታወጀንጉሥ ቻርልስ “ስለ ሕክምናቸው ሙሉ እምነት ያላቸው ሲሆን ወደ የህዝብ ኃላፊነታቸው ለመመለስ በተቻለ ፍጥነት ጉጉት አላቸው” ሲል ቤተመንግሥቱ አመልክቷል።
ባለፈው ወር ከዚህ በተለየ መንገድ ህክምና በተደረገላቸው ወቅት የዕጢ እብጠት መከሰቱ አሳሳቢ ሆኖ እንደነበር በኪንግሃም ገልጿል።
ባለፈው ሕክምና ወቅት “የተለየ አሳሳቢ ጉዳይ ታይቷል” ብሏል ቤተመንግሥቱ።