እነ አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ቀረቡ

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪ አቶ በቀለ ገርባ

ሰሞኑን ኦሮምያ ውስጥ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎች እነ አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ሰሞኑን ኦሮምያ ውስጥ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎች እነ አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፌደራሉ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

የችሎቱን ሂደት በቀጥታ ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ የነበረው መለስካቸው አምሃ ወደ ውስጥ እንዲገባ ባይፈቀድለትም ከችሎቱ ሲወጡ ያገኛቸው አቶ በቀለ ገርባ የሃያ ስምንት ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደተጠየቀባቸው ገልፀዋል።

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪ አቶ በቀለ ገርባ

የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ከሆኑት ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር ዛሬ ችሎት የቀረቡት የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋና የወጣቶች ሊግ ፀሐፊው አቶ አዲሱ ቡላላ መሆናቸውን መለስካቸው ማረጋገጡንና በእነ አቶ በቀለ ገርባ መዝገብ የተከሰሱት ግን 21 ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን ዘግቧል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

እነ አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ቀረቡ