ለቀድሞ መሪዎች መታሠቢያ መቆሙ "ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው" ተባለ

  • እስክንድር ፍሬው

አፍሪካ ሕብረት

የአፍሪካ ሕብረት ለሁለት የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎች የመታሠቢያ ሃውልት እንዲቆም መወሰኑ ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ለሁለት የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎች የመታሠቢያ ሃውልት እንዲቆም መወሰኑ ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንዳብራሩት ውሳኔው ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የተሰጠ ሽልማት ነው፡፡

ለሁለት ቀናት የተካሄደውና በትናንትናው ዕለት የተጠናቀቀው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ነው፣ ለሁለት የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎች መታሠቢያ እንዲቆም የወሰነው፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ

መታሰቢያ እንዲቆምላቸው የተወሰነው ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው፡፡ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንደዚሁም ለአፍሪካ ሕብረት ምሥረታ እና ማጠናከር ለአበረከቱት አስተዋፅዖ፡፡

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ለቀድሞ መሪዎች መታሠቢያ መቆሙ "ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው" ተባለ