አዲስ አበባ —
በአንዳንድ ሀገራት ያሉ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች አሳሳቢ መሆናቸውን ቀጥለዋ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡ ይሄም ሆኖ በአህጉሪቱ ተስፋ ሰጭ ሁኔታዎች መኖራቸውን በሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ ላይ የተናገሩት የኮሚሺኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ አስረድተዋል፡፡
ሌላው በጉባዔው መክፈቻ ላይ የተናገሩት የፊሊስጤም አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሙሐሙድ አባስ ከእስራኤል ሰላም ለማምጣት በፕሬዚዳንት ትራምፕ የቀረበው የሰላም ሀሳብ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዛሬ በአዲስ አበባ ዋና ፅ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ እንደተለመደው ያለፉት ወራት ክንውኖች ስኬቶችና አሳሳቢ ሁኔታዎች የተዳሰሱበት ነው፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ