የመርዓዊ ከተማን ጨምሮ በአማራ ክልል ሦስት ስፍራዎች፣ ባለፈው ጥር ወር በትንሹ 66 ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።
በመርዓዊው ጥቃት፣ “ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል” በሚል ከተገደሉት ቢያንስ 45 ሲቪሎች በተጨማሪ፣ “የፋኖ አባላት ናቸው” በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችም እንደተገደሉ ኮሚሽኑ ገልጿል።
SEE ALSO: መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዐማራ ክልል ላይ ያወጣውን ሪፖርት አጣጣለበጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዲሬክተር ዶ/ር ሚዛኔ አባተ ጠቁመዋል፡፡ ከሌሎችም አካባቢዎች ለኮሚሽኑ በደረሱ የግድያ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደኾነ አክለው ጠቅሰዋል።
SEE ALSO: በመርዓዊ ከተማ ከ80 በላይ ሲቪሎች መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታወቀየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በበኩሉ፣ በመርዓዊው ጥቃት የተገደሉ ሲቪሎች ቁጥር ከ80 በላይ እንደሚኾን መግለጹ ይታወቃል፡፡ መግለጫውን ተከትሎም የአሜሪካ መንግሥት ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር፡፡ ከመንግሥት በኩል ስለ ጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
SEE ALSO: አሜሪካ በመርዓዊ ከተማ በተፈጸመው ግድያ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀችዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።