የባሕር ዳር የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጠየቁ

የዐማራ ክልል ርእሰ መዲና ባሕር ዳር ከተማ

Your browser doesn’t support HTML5

የባሕር ዳር የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጠየቁ

በትጥቅ ግጭት ውስጥ በሚገኘው የዐማራ ክልል ርእሰ መዲና ባሕር ዳር ከተማ፣ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሔደውን የሰላም ጉባኤ የተሳተፉ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ በግጭቱ ዐውድ ውስጥ የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዜጎች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

SEE ALSO: ኢሰመኮ የዐማራ ተወላጆችን እስራት አወገዘ

ተሳታፊዎቹ፣ በሰላም ጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት ባለዐሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ፣ መንግሥት ታሳሪዎቹን በምሕረት እና በይቅርታ መፍታቱ፣ “ለክልሉ ዘላቂ ሰላም የበኩላቸውን እንዲወጡ ያስችላል፤” ብለዋል፡፡

ጉባኤውን በአዘጋጀው በክልሉ መንግሥት እና በተሳታፊዎች መካከል፣ እስረኞቹ እንዲፈቱ መግባባት ላይ ስለመደረሱ ግን የተገለጸ ነገር የለም፡፡

SEE ALSO: መርማሪዎችና ጋዜጠኞች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ ተጠየቀ

የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ፣ በሰላም ጉባኤው የአቋም መግለጫ ላይ የቀረበው ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በዐማራ ክልል ላይ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ማብቃቱን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ እንደሚያንጸባርቅ፣ በኮሚሽኑ የሪጅን ዲሬክተር አቶ ዓለሙ ምሕረት አመልክተዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዛሬ ያበቃል

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ ፓርቲን በመወከል ከክልሉ ተመርጠው ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቡት አቶ አበባው ደሳለው፣ መንግሥት ራሱ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ፣ ታሳሪዎችን ለመፍታት ዕቅድ እንዳለው የሚያሳይ ነው፤ ብለዋል፡፡