በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት በድጋሚ ተዘጋ


ዐማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት በድጋሚ ተዘጋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00

ዐማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት በድጋሚ ተዘጋ

በዐማራ ክልል፣ ለሦስት ሳምንታት ያህል ስልክ ተቋርጦ የሰነበተባቸው፣ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች፣ ከትላንት ማክሰኞ ከቀትር በኋላ ጀምሮ፣ የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ፣ የዘመዶቻቸውን ደኅንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው፣ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ እና በዙሪያው፣ ከትላንት ከቀትር በኋላ ጀምሮ፣ የስልክ አገልግሎት እንደማይሠራ አረጋግጠናል፤ ብለዋል፡፡

በአካባቢው፣ ግጭቶች ዳግም ስለመቀስቀሳቸው መረጃ እንዳላቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የስልክ አገልግሎቱ በድጋሜ የተቋረጠው፣ ከዚኹ ጋራ በተያያዘ ሳይኾን እንደማይቀር ጠቁመዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩን፣ በእጅ ስልካቸው እና በዋትሳፕ መተግበሪያ መረጃ እንዲሰጡን ብንደውልላቸውም፣ ስልካቸው ባለመነሣቱ ምክንያት ምላሻቸውን ለማካተት አልቻልንም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በባሕር ዳር ዙሪያ ሰባታሚት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፣ ከትላንት ጀምሮ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል፣ የተኩስ ልውውጥ እንደነበርና በዚኽም ሰዎች እንደተገደሉ፣ የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG