ዋሺንግተን ዲሲ —
ከሁለት ሣምንታት በፊት በያኔው የዚምባብዌ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከሥልጣን ከተባረሩ በኋላ ለደኅንነታቸው በመስጋት በጎረቤት ሃገር የቆዩት የቀድሞው ምክትል ፕሬዘዳንት ኤመርሰን ናንጋግዋ ወደ ሃራሬ ተመልሰዋል።
በዚምባብዌ “አዲስ” ሲሉ የጠሩትን ዲሞክራሲ ለማምጣት ቃል ገብተዋል።
ኤመርሰን ናንጋግዋ በነገው ዕለት ይፈፅማሉ የተባለውን ቃለ መሃላ ሕዝቡ እየተጠባበቀ ባለበት ባሁኑ ወቅት ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ ቻይናና ሌሎች የዓለምቀፉ ማኅበረሠብ አባላት ሃገሪቱ ወደፊት በምታደርገው ጉዞ ለመርዳት ቃል ገብተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ