በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዞን አመራሮች በሕዝቡ ታስረው እንዲቆዩ ተደረገ


በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ፌስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ
በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ፌስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ

በአማራ ክልል በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ቅላዥ ከተማ፤ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ያነሱ ነዋሪዎች በአደራ ፖሊስ ጣቢያ ያስቀመጧቸው የዞን አመራሮችና የፀጥታ ኃላፊዎች በመለቀቃቸው ግጭት ተፈጠሮ አራት ሰዎች ቆሰሉ። ነዋሪዎችና የዞን አመራር ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

በአማራ ክልል በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ቅላዥ ከተማ ነዋሪዎች ያነሱት የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለረጅም ዓመት ሊመለስላቸው ባለመቻሉ የዞን አመራሮችና የፀጥታ ኃላፊዎችን ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንዲቆዩ ማድረጋቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ከፍተኛ የክልል ባለሥልጣናት መጥተው እሲኪያነጋግሩን አመራሮቹን አስሮ እንዲያቆይ ኃላፊነት የተሰጠው ፖሊስ ጣቢያ በድብቅ እንዲወጡ አድርጎብናል በማለታቸውም ከፖሊስ ጋራ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል።

የአዊ ብሔረሰብ ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው፤ ምንም የመብራት አገልግሎት የሌለባት ብቸኛ ወረዳ

የሕዙን ጥያቄ እኛም እንጋራዋለን ብለዋል።አመራሮቹን በተመለከተም አሁን ተለቀዋል በውይይት ይፈታል ተብሏል። ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ የዞን አመራሮች በሕዝቡ ታስረው እንዲቆዩ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:40 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG