በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰንዓ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን በጦርነት ተጠምደዋል


የመን
የመን

የመን ዋና ከተማ ሳንዓ ውስጥና በአካባቢዋ የቀድሞ አጋሮች በነበሩት የሁጢ አማፂያንና በቀድሞው ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳለህ ታማኝ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰውና ላለፉት በርካታ ቀናት እየተካሄደ ባለው የከበደ ውጊያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው እየተሰማ ነው።

የመን ዋና ከተማ ሳንዓ ውስጥና በአካባቢዋ የቀድሞ አጋሮች በነበሩት የሁጢ አማፂያንና በቀድሞው ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳለህ ታማኝ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰውና ላለፉት በርካታ ቀናት እየተካሄደ ባለው የከበደ ውጊያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው እየተሰማ ነው።

በፕሬዚዳንት አብድ ራቦ መንሱር ሃዲ የሚመራውን መንግሥት በምትደግፈው በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ዓለምአቀፍ ወታደራዊ ጥምረት በግንባር ይፋለሙ በነበሩት ኃይሎች መካከል የተፈጠረው መከፋፈልና ግጭት የሃገሪቱን ፖለቲካ ወዳልተጠበቀ አቅጣጫ ሊቀይረው እንደሚችል ተነግሯል።

ሰንዓ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን በጦርነት ተጠምደዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:53 0:00

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባባሰው ጦርነት በዋና ከተማዪቱና በአካባቢዋ ችግር ላሉ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ በማድረጉ ወገኖቹ በአፋጣኝ ውጊያቸውን እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ጥሪ አሰምተዋል።

ሰንዓ ውስጥ ኃይል በሚባል አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ የሚያስፈራ እንደሆነ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

እዚያው ሰንዓ የሚገኙትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ አስተባባሪውን ጄሚ ማክጎልድብሪክን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት እያደረግን ነን፤ የሚሉትን እንዳገኘን ዌብሳይታችን እንዲሁም ማኅበራዊ መገናኛ ገፆቻችን ላይ እናወጣለን፤

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሰንዓ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን በጦርነት ተጠምደዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG