በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰንዓ ጦርነት ከ230 በላይ ሰው ተገደለ

በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አስተባባሪ ጄሚ ማክጎልድበርግ
በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አስተባባሪ ጄሚ ማክጎልድበርግ

የመን ዋና ከተማ ሰንዓ ውስጥ ባለፉት አራት ቀናት በተካሄዱ ከባድ ውጊያዎች ከ230 በለይ ሰው መገደሉንና ቁጥራቸው ከአራት መቶ በላይ የሆኑ ሌሎች ሰዎች መጎዳታቸውን በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ አስተባባሪ ለቪኦኤ ገለፁ።

የመን ዋና ከተማ ሰንዓ ውስጥ ባለፉት አራት ቀናት በተካሄዱ ከባድ ውጊያዎች ከ230 በለይ ሰው መገደሉንና ቁጥራቸው ከአራት መቶ በላይ የሆኑ ሌሎች ሰዎች መጎዳታቸውን በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ አስተባባሪ ለቪኦኤ ገለፁ።

ሰንዓ ውስጥ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ቢመስልም ውጥረትና ሥጋት አሁንም እንደበረታ መሆኑን ከተማዪቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ገልፀዋል።

በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አስተባባሪ ጄሚ ማክጎልድበርግ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ቀይ መስቀል ዛሬ፤ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ባካሄደው ምዝገባ ከታወቀው የሟቾችና የቁስለኞች ቁጥር በተጨማሪ ሕክምና ጣቢያዎች ሳያይዋቸው የተቀበሩ፣ ወይም መረጃቸው ለቀይ መስቀል ያልደረሰ ሰዎች ስለሚኖሩ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል አመልክተዋል።

ከሕይወትና ከአካል ጉዳቱ ሌላ በሮኬት፣ በቦምብ፣ በከባድ መሣሪያዎችና በአየር ድብደባ ብዙ ሕንፃዎች መፈራረሣቸውን ማክጎልድብሪክ ጠቁመው ባለፈው ሌሊት ብቻ ሰንዓ ላይ ከሃያ አምስት በላይ የአየር ድብደባዎች መፈፀማቸውን ገልፀዋል።

ከሁለት ሺህ ሰው በላይ የፈጀው ኮሌራ አሁንም ሥጋት እንደሆነ መሆኑንና ነኂህ ውኃ ማቅረብ ትልቁን ትኩተት የሚሠጡት ሥራ እንደሆነም አስተባባሪው አክለው አስረድተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሰንዓ ጦርነት ከ230 በላይ ሰው ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:53 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG