በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ያማሞቶ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ከባለሥልጣኖች ጋር ተነጋገሩ

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሞቶ
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሞቶ

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሞቶ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ከሌሎች የሀገሪቱ ባለሥልጣኖች ጋር ተገናኝተው ስለጋራ ጉዳዮች ተነጋገረዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሞቶ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ከሌሎች የሀገሪቱ ባለሥልጣኖች ጋር ተገናኝተው ስለጋራ ጉዳዮች ተነጋገረዋል።

ኤርትራ ካለው የዲፕሎማቶች ማኅበረሰብና ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሠራተኞችም ጋር ተነጋግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያና ኤርትራ ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ማበረታታቱን ትቀጥላለች። ሂደቱን ለማገዝም ዝግጁ ናት ይላል ሆለርስ ማሪዮን የተባሉ አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ተወካይ ኤርትራ ለሚገኘው ዘጋብያችን የላኩት መግለጫ።

የኤርትራ የማስታወቅያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀልም በአምባሳደር ያማሞቶ የተመራ የዩናይትድ ስቴትስ መልዕክተኞች ቡድን በአስመራ የሦስት ቀናት ጉብኝት ማካሄዱን በትዊተር ገልፀዋል።

ያማሞቶ ዛሬና ነገ ጂቡቲ በሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስና የጅቡቲ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተዋል። ውይይቱ ስለፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ዕርዳታና የፀጥታ ትብብርን በሚመለከት በየዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን መግለጫው አክሏል።

አምባሳደር ያማሞቶ በመጪው ሀሙስ ወደ ኢትዮጵያ የማራሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG