በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶናልድ ያማሞቶ ለሥራ ጉብኝት ኤርትራ ገብተዋል

ፎቶ ፉይል:-የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ ዋና ምክትል ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ
ፎቶ ፉይል:-የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ ዋና ምክትል ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ ዋና ምክትል ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ኤርትራ ገብተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች የውጭ ጉዳይ ዋና ምክትል ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ኤርትራ ገብተዋል።

ረዳት ሚኒስትሩ አሥመራ የገቡት ትናንት ሲሆን በሁለቱ ሃገሮች መካከል ባሉ ግንኙነቶች ላይ ከመንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩና አሥመራ ከሚገኙ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አባላት ጋር እንደሚገናኙ ተገልጿል።

አምባሳደር ያማሞቶ የአሥመራ ጉዟቸውን ከነገ በስተያ ረቡዕ ሲያጠናቅቁ ወደ ጂቡቲ ተጉዘው ሃገራቸው ከጂቡቲ ጋር ባሏት የፖለቲካ፣ የምጣኔ ኃብት፣ የእርዳታና የፀጥታ ትብብር ግንኙነቶች ላይ በሚመክረው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የዩናይትድ ስቴትስን ቡድን መርተው እንደሚገኙ ታውቋል።

ሚስተር ያማሞቶ የፊታችን ዐርብ፤ ሚያዝያ 19/2010 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ ባሏቸው የጋራ ጥቅሞችና ሥጋቶች ላይ ከመንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚመክሩ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባወጣው አጭር ዘገባ ጠቁሟል።

ሚስተር ያማሞቶ ባለፈው ኅዳር ወደ አካባቢው ተጉዘው በነበረ ወቅት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን ሃገራቸው በቁርጠኛነት እንደምትሠራ አስታውቀው ነበር።

የአምባሳደር ያማሞቶን የትናንትና የዛሬን የኤርትራ ቆይታ አስመልክቶ ዝርዝርና የቅርብ መረጃ ለማግኘት የተለያዩ ጥረቶችን ብናደርግም ለጊዜው አልተሣካም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG