በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከፈረንሳይ ጋር አዲስ የትብብር ግንኙነት ለመጀመር ፍቃደኛ ነኝ” ፕሬዝዳንት ሺ


የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓሪስ
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓሪስ

ሺ በአውሮፓ የሚያደርጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት ለመጀመር ፈረንሳይ ገብተዋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ትላንት ሰኞ በኤሊዜ ቤተ መንግስት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ነው ‘ከፈረንሳይ ጋር አዲስ የትብብር ግንኙነት ለመጀመር መፍቀዳቸውን’ የተናገሩት።

“አሁን በሚታየው የክፍለ ዘመኑ ምስቅልቅል ውስጥ ቻይና እና ፈረንሣይ ገለልተኝነታቸውን ማረጋገጥ፤ አዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ወይም በጎራዎች መካከል ሊፈጠር የሚችል ግጭት በጋራ መከላከል፤ የጋራ መግባባትን አጥብቆ መሻት እና ልዩነት በበዛበት ዓለም በጋራ አብሮ መኖርን በጋራ ማራመድ መቻል አለባቸው” ሲሉ ሺ ለፈረንሣይ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ሺ ፓሪስ ላይ መጀመሪያ ከማክሮን ጋር እና በመቀጠልም ሰፋ ባሉት የአውሮፓ ሕብረት ስጋቶች ዙሪያ ለመነጋገር ከሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አርሱላ ቫን ደር ሊን ጋር ተገናኝተዋል። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ባይደን ራሳቸው ከሚያደርጉት ጉዞ አንድ ወር አስቀድሞ የመጣውን ይህን ሺ ከፈረንሳይ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ዋሽንግተን በቅርበት እንደምትከታተለው ተመልክቷል።

ማክሮን ባለፈው ዓመት በሚያዝያ ወር ወደ ቻይና ያደረጉትን ጉዞ የተከትለው የሺ ጉብኝት ፈረንሳይ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመሰረቱበት 60ኛ ዓመት ጋርም ተገጣጥሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG