በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ፈረንሣይን እየጎበኙ ነው


የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓሪስ
የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓሪስ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግን ዛሬ ሰኞ ፓሪስ በሚገኘው ኢሊዜ ቤተ መንግሥት በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ፕሬዝዳንት ሺ ያልተለመደውን መንግሥታዊ ጉብኘት የጀመሩት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ላየን ጋር በመወያየት ነው፡፡

የቻይና ፕሬዚደንት ዓለም አቀፍ ውጥረት በነገሠበት በዚህ ወቅት ግንኙነቶችን መልሶ ለመመስረት በሚያደርጉት በአውሮፓ ጉዟቸው ፈረንሳይ የመጀመሪያቸው ናት፡፡

በፈረንሳይ የሁለት ቀናት ጉብኝት የሚያደርጉት ሺ ሩሲያ የዩክሬን ጦርነትን እንድታቆም ያላቸውን ተጽዕኖ እንዲጠቀሙ ማክሮን ግፊት እንደሚያደርጉ ተጠብቋል፡፡

መሪዎቹ በኤሌክትሪክ መኪኖች፣ በኮኛክ እና በመዋቢያ ምርቶች ዙሪያ በሚነሱ የንግድ ውዝግቦች ላይም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሺ በአውሮፓው ቆይታቸው በዋነኝነት የሚያተኩሩት በአውሮፓ ህብረት እና በቻይና መካከል ፍትሃዊ የንግድ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ነው፡፡

በቻይና የሚደጎሙ ኢንዱስትሪዎች የአውሮፓ ገበያዎችን ውድ ባልሆኑ ዕቃዎች በማጥለቅለቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ከሺ ጉብኝት አስቀድሞ ማክሮን እና ቮን ደር ሌየን በሰጡት መግለጫ ውይይቱ በአውሮፓ ህብረት እና ቻይና ግንኙነት ዙሪያ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ቮን ደር ሌየን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የንግድ መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀምን ጨምሮ፣ የአውሮፓ ኅብረት ኢኮኖሚውን እና ደህንነቷን ለመጠበቅ ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ለፍትሃዊ ሰጥቶ መቀበል አጠቃቀም እና የገበያ ተደራሽነትን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የቻይናው መሪ ነገር ማክሰኞ ወደ ሰርቢያ እና ሃንጋሪ ያቀናሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG