በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤችአይቪ ሥርጭት በኢትዮጵያ 1.2 ከመቶ ነው


ኢትዮጵያ ውስጥ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኘው ሰው ቁጥር ከ718 ሺህ በላይ መሆኑንና ከእነዚህም መካከል ሕክምና እየተከታተሉ ያሉት 69 ከመቶ የሚሆኑት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅሕፈት ቤት አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኘው ሰው ቁጥር ከ718 ሺህ በላይ መሆኑንና ከእነዚህም መካከል ሕክምና እየተከታተሉ ያሉት 69 ከመቶ የሚሆኑት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅሕፈት ቤት አስታወቀ።

ፅሕፈት ቤቱ ዛሬ ማምሻውን ለቪኦኤ በሰጠው መግለጫ ሥርጭቱ አሁንም ዕድሜአቸው ከ15 እስከ 24 በሆኑ ወጣቶች ዘንድ የሰፋ መሆኑን አመልክቶ ኤድስን በመጭዎቹ 12 ዓመታት ውስጥ የኅብረተሰቡ ችግር ወደማይሆንበት ደረጃ ለማውረድ ጥረቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ መከላከልን፣ ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረግን፣ የኮንደም ሥርጭትን ማጠናከርና ማስፋትን፣ የወንድ ልጆችን ግርዛት ማበረታታትን ያካተተ ባለአምስት መስክ ስትራተጂ ሥራ ላይ አውላ እየተንቀሳቀሰች መሆኗን የፅሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብረሃም ገብረመድኅን አመልክተው ከመጋለጥ በፊት የሚሰጥ የመከላከያ መድኃኒትን ማቅረብ በአቅም ምክንያት ገና በሚያጠረቃ ሁኔታ አለመጀመሩን ተናገረዋል።

ከውጭ የሚገኘው እርዳታ መቀነሱንና ያለውም የሚውለው ሙሉ በሙሉ ለሕክምና መሆኑንና ለመከላከል ሥራዎች ሃገሪቱ በአመዛኙ በሃገር ውስጥ ጥሪት ላይ ለመመርኮዝ መምረጧን ምክትል ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በመላው ዓለም በኤድስ ምክንያት የሚሞቱት ከወንዶች ይልቅ ሴቶች መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ጠቁሟል።

ይህም የሚሆነው አንድም የሚመረመረው ወንድ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ፤ አልያም ከሴቶች ይልቅ ወንዶች መድኃኒትና ሕክምና የሚያገኙ በመሆናቸው መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል።

የዘንድሮው የዓለም ኤድስ ቀን ኢትዮጵያ ውስጥ “አሁንም ትኩረት ለኤችአይቪ/ኤድስ” በሚል መርህ በአማራ ክልል ኮምበልቻ ከተማ በተከናወኑ ሥነ-ሥርዓቶች ታስቦ ውሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኤችአይቪ ሥርጭት በኢትዮጵያ 1.2 ከመቶ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:14 0:00
የዓለም ኤድስ ቀን - ከአቶ አብረሃም ገብረመድኅን፤ የሃፕኮ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:44 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG