በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ወሎ የካቤና ለጎጎራ አካባቢ ኗሪዎች ጥያቄ

በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ስር የሚገኙት የካቤና ለጎጎራ አካባቢ ኗሪዎች የካቤ የቀድሞ ወረዳነት ተመልሶልን ራሳችንን ማስተዳደር አለብን የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጥያቄውን ተከትሎ የወረኢሉ ወረዳነት ሊታጠፍ ይችላል የሚል ጭምጭምታ በመሰራጨቱ በወረዳው ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ስር የሚገኙት የካቤና ለጎጎራ አካባቢ ኗሪዎች የካቤ የቀድሞ ወረዳነት ተመልሶልን ራሳችንን ማስተዳደር አለብን የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጥያቄውን ተከትሎ የወረኢሉ ወረዳነት ሊታጠፍ ይችላል የሚል ጭምጭምታ በመሰራጨቱ በወረዳው ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡

ውጥረቱ አመራሮችን ከሥልጣናቸው አሰናብቶ ግጭቶችን እስከማስተናገድ የደረሰ ነበር፡፡ ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹ የአካባቢው ኗሪዎች “ከሁሉም የሚልቀው የመንግሥት መዋቅሩ ከስድስት ወራት በላይ መደበኛ ተግባሩን እያከናወነ ባለመሆኑ ለከፋ ችግር መዳረጋችን ነው” - ብለዋል፡፡

የዞኑ አሰተዳደር መንግሥታዊ መዋቅሩ እንዲቀጥል ማድረጉን ቢያስታውቅም የወረዳው ኗሪዎች በአንድ በኩል መዋቅሩ በተጠናከረ መልኩ ሥራውን እየሰራ አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ የተቋቋመው መዋቅር አይወክለንም የሚሉ አሉ፡፡ መስፍን አራጌ ከሥፍራው ዘገባ ልኳል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በደቡብ ወሎ የካቤና ለጎጎራ አካባቢ ኗሪዎች ጥያቄ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:01 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG