No media source currently available
በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ስር የሚገኙት የካቤና ለጎጎራ አካባቢ ኗሪዎች የካቤ የቀድሞ ወረዳነት ተመልሶልን ራሳችንን ማስተዳደር አለብን የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጥያቄውን ተከትሎ የወረኢሉ ወረዳነት ሊታጠፍ ይችላል የሚል ጭምጭምታ በመሰራጨቱ በወረዳው ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡