በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወልቃይት ጉዳይ የተጠናቀረ ዝግጅት


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በወቅቱ የኮሚቴው ዋና ጸሐፊና የወጣቶች ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አደራጀው ዋኘው እዚህ አሜሪካ የሚገኙ በመሆናቸው ጽዮን ግርማ ይህን ጥያቄ መነሻ አድርጋ አነጋግራቸዋለች።

በሰሜን ኢትዮጵያ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሕዝብ፤ “የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ” በሚል አስተባባሪ 20 ዓባላትና ዘጠኝ ስራ አስፈፃሚ ያሉ ኮሚቴ አቋቁመው ከታኅሣሥ 27/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር፣ ከዛም ይህ ጉዳይ ተቃውሞዎችን ቀስቅሶ ለበርካቶች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ንብረት መውደምና እስር ምክንያት እንደነበር የአሜሪካን ድምጽ ጨምሮ በበርካታ ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ሲዘግቡት እንደቆየ ይታወሳል።

ለዚህ ዘገባ መነሻችን ከሁለት ሳምንት በፊት በአማራ ክልል ከተካሄደው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በኋላ የመጀመሪያ የሆነው የካቤኔ ሹም ሽር ሲካሄድ በወቅቱ ያነጋገርናቸው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ያነሱት ተቃውሞው የተቀሰቀሰበትን ዋናውን የወልቃይት ጉዳይና ለሌሎችንም የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጥ “ግምገማና ጥልቅ ተሃድሶ አድርገናል” ማለት ፋይዳ የለውም ማለታቸውና “አሁን የወልቃይት ጉዳይ ምን ደረሰ?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ነበር።

በወቅቱ የኮሚቴው ዋና ጸሐፊና የወጣቶች ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አደራጀው ዋኘው እዚህ አሜሪካ የሚገኙ በመሆናቸው ጽዮን ግርማ ይህን ጥያቄ መነሻ አድርጋ አነጋግራቸዋለች።

የመንግስት ምላሽም በዘገባው ተካቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በወልቃይት ጉዳይ የተጠናቀረ ዝግጅት
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:52 0:00

XS
SM
MD
LG