በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወላይታ ዞን ም/ቤት ጉባዔ


ወላይታ ብቻውን እንጂ ከ«ኦሞቲካ ቤተሰብ» ቋንቋ ተናጋሪዎች ከጋሞና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ለመካለል እንደማይፈልግ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ መወሰኑን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ መቀመጫውን በሰሜን አሜሪካ ያደረገው የወላይታ፥ የዳውሮና የጋሞ ተወላጆችን በማካተት የተመሠረተው የኦሞ ኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል “በቋንቋ፥ ታሪክና በባሕል አብሮ ተስማምቶ በመኖር የሚታወቀውን የኦሞ አካባቢን ሕዝብ ለበለጠ የጋራ ዕድገት በአንድነት ማደራጀት ሲገባ ይልቁንስ አብሮነትን የሚሸረሽር ሃሳብ በአንዳንድ የወላይታ ፖለቲከኞችና በህወሓት/ኢህዴግ/ እየተንፀባረቀ ነው” ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የወላይታ ዞን ም/ቤት ጉባዔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00


XS
SM
MD
LG