በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የሚበሉት አጥተው ነው የሚሰደዱት" ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው እና ኢብራሂም ሻፊ


ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው እና ኢብራሂም ሻፊ
ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው እና ኢብራሂም ሻፊ

ስደት ብዙ መልክ አለው፡፡ ሰዎች በሥራ እና በትምሕርት ምክንያት ከተወለዱበትና ካደጉበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በመዛወር በፍላጎታቸው አዲስ ኑሮን ይጀምራሉ፡፡ የተማሩ ሰዎች በተማሩበት ትምሕርት ልክ የተመቻቸ ነገር ማግኘት ሲያቅታቸውም ይሰደዳሉ፡፡ ይህንንም ምሑራዊ ስደት እንለዋለን፡፡ እንዲሁም ሰዎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት አገር ጥለው ይሰደዳሉ፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለምን ይሰደዳሉ? ይህ ዘገባ የሚለው ይኖረዋል።

በ2015 ዓ.ም የተደረጉ ጥናቶች በዓለማችን የሰዎች ዝውውር ቁጥር 250 ሚሊዮን እንደደረሰ ያመለክታሉ። ይህ ቁጥር በ2000 እ.አ.አ. በነበረ ጥናት 175 ሚሊዮን፣ በ1990 ዓ.ም በነበረ ጥናት ደግሞ154 ሚሊዮን እንደነበረ እነዚሁ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ቁጥር በጊዜ ሂደት ሲታይ ሰዎች ተዘዋውሮ የመኖር ፍላጎታቸው እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት በስደት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለአስከፊ ችግር ተጋልጠዋል። በተለይም ወጣት ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ መንገድ በሚደረግ ዝውውር በውሀ ጥም፣ በረሀብ፣ በአውሬ በመበላት፣ ኢሰብዓዊ በሆኑ ሕገወጥ የድንበር አሸጋጋሪዎችና በሰው የመግደል ወንጀል በተሰማሩ ደላሎች እና በሌሎችም ወንጀሎኞች እጅ በመውደቅ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ይገኛል።

Ethiopian migrants look through a fence as they wait to be evacuated at a departure center in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia and Yemen, Wednesday, March 21, 2012.
Ethiopian migrants look through a fence as they wait to be evacuated at a departure center in the western Yemeni town of Haradh, on the border with Saudi Arabia and Yemen, Wednesday, March 21, 2012.

በዚህም ምክንያት ለአካል ጉድለት፣ ለአእምሮ መታወክ ባስ ብሎም አንገታቸውን እስከመቀላት ደርሰዋል፡፡ በርካታቶች በመንገድ በሚያጋጥማቸው ፍጹም ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ባሰቡበት ቦታ ሳይደርሱ ቀርተዋል፡፡ በአስገድዶ መደፈር ክብርን በሚነካ ስብዕናቸውን በሚጎዳ ሁኔታ ሰለባ ሆነዋል።

የተለያዩ ጥናቶች እና ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት አሁንም ይህ ሕገ ወጥ ስደት በተለያ መልኩ እንደቀጠለ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ለምንድነው የሚሰደዱት?

ኢብራሂም ሻፊ ይባላል፡፡ መምሕር ነበር፡፡ በትምሕርት ቢሮ ውስጥ በአስተዳደር ሥራ አገልግሏል፡፡ ለአሥራ ሦስት ዓመት ጋዜጠኛም ነበር፡፡ አሁን በስደት ኬንያ ይገኛል፡፡ ስደትን እስከተቀላቀለበት እስካለፈው ዓመት ድረስ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል አዘጋጅ ነበር፡፡በዚህ ቆይታው ከስደት እና ወጣቶች ጋር በተያያዘ በርካታ መረጃዎች አሉት፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች አብዛኛው ወጣት ለስደት ከሚወጣባት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወይም ጨርቆስ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ነው ፡፡ “ቂርቆስ አካባቢ በንጽጽር ከሌሎች የአዲስ አበባ ከተሞች ጋር ሲተያይ በኑሮ ዝቅ ያሉ ሰዎች የሚኖሩበት፤ ምግብን ጨምሮ በርካታ ችግሮች ያሉበት አካባቢ ነው›› ይላል ኢብራሂም፡፡ ጽዮን ግርማ ወጣቶቹ ለምን በብዛት ይሰደዳሉ?ስትል ትጠይቀዋለች፡፡

ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) ከስደት ተመላሾች ማነጋገሩን ጠቅሶ ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያውያ አሁንም በሦስት በሮች የሚያደርጉትን ስደት አላቆሙም፡፡ በምስራቅ በር በሚባለው መንገድ ከኢትዮጵያ በአፋር በኩል አድርገው ጀልባ በመሳፈር ወደ የመን ከዚያ ወደ ሳውዲ አረቢያ ይጓዛሉ፡፡

በደቡብ በር በሚባለው መንገድ ደግሞ በኬንያ በኩል ታንዛኒያ ዙምባብዌ ማላዊ አቆራርጠው ደቡብ አፍሪካ ይገባሉ፡፡ ከዚያም የተወሰኑት እዚያው ይቀራሉ፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ወደ አውሮፓ እና በሜክሲኮ አድርገው ወደ አሜሪካ ለመሻገር ጥረት ያደርጋሉ፡፡

ነገር ግን አብዛኞቹ ካሰቡበት አገር ሳይደርሱ እንደመሸጋገሪያነት ባረፉበት አገር ተይዘው ለብዝበዛ፣ለእስራት፣ለግዳጅ ሥራ እና ለመታገት ይዳረጋሉ፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ አድርጎ ወደ ደቡብ አፍሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚጋዙ፤እንዲሁም ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው የመን ሊገቡ ሲሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚሞቱ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች ቁጥር እያደገ መጥቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን በተለይ ወጣቶች ግን አሁንም መሰደድን አላቆሙም፡፡ ለምን? ዶር ደረሰ ጌታቸው የዶክትሬት መመረቂያ ጥናቱን የሠራው ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ምስራቅ አፍሪካ ስለሚሰደዱ ሰዎች ነው፡፡ ጽዮን ግርማ ይህንኑ በተመለከተ አነጋግራዋለች፡፡እናንተ አድማጮቻችን በማሕበራዊ ሚዲያ ፌስ ቡክ ላይ ይህንኑ የውይይት ርእስ አስመልክቶ የሰጣችኋቸው አስተያየቶችም ዛሬ ይቀርባሉ፡፡ሁሉንም እንግዶች አነጋግራ ፕሮግራሙን የሠራችው ጽዮን ግርማ ነች፡፡

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

የፎስ ቡክ ተሳታፊዎች የሰጣችሁት አስተያየትም ተካቷል።

"የሚበሉት አጥተው ነው የሚሰደዱት"
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG