በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት ላይ የውጭና የውስጥ ምላሾች


ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ይፋ ያደረጉት የ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት በሃገር ውስጥም፣ በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጭም እያነጋገረ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ይፋ ያደረጉት የ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት በሃገር ውስጥም፣ በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጭም እያነጋገረ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወታደራዊ ኃይላቸውንና የደኅንነት ክንፋቸውን፣ በተለይ የሕግ አስከባሪውን ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ ማጠናከር ነው ሃሣባቸው፡፡

በአንፃሩ ደግሞ የውጭ እርዳታ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ለዓለምአቀፍ ድርጅቶችና ተቋማት ስትለግስ የቆየችው ክፍያ፣ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ በጀት፣ የውጭ ጉዳዮች፣ ጥበብ፣ መዘክሮችና የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ከባዱ የቆረጣ መቀስ ሊውልባቸው የተነደፈበት ረቂቅ ነው ፕሬዚዳንቱ ትናንት ለተወካዮች ምክር ቤታቸው የላኩት፡፡

ይህንኑ የበጀት ሃሣባቸውን ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑን ቴኔሲ ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው የዘመቻ ዓይነት ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሲያብራሩ ጦራቸውን ከምቼውም ጊዜ የሰፋ፣ የተሻለና የጠነከረ እንደሚያደርጉት ገልፀዋል፡፡

የተወካዮች ምክር ቤቱ የአብላጫዎቹ መሪና አፈጉባዔም የሆኑት የዊስከንሰኑ ሪፐብሊካን እንደራሴ ፖል ራያን አዲሱን የትረምፕ የ2018 ዓመት በጀት ረቂቅ እንደሚደግፉ ሲናገሩ ወታደራዊ ኃይሉን እንደገና በመገንባቱ ሃሣብ መበረታታቸውን አመልክተዋል፡፡

ዴሞክራቶቹና ሌሎችም ይህ የበጀት ረቂት እምብዛም ያልጣማቸው አስተያየት ሰጭዎች “የአሜሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው ከጦር ኃይሏ ብቻ አይደለም” ይላሉ፡፡

የተወካዮች ምክር ቤቱ የሕግ መምሪያ የአናሳዎቹ እንደራሴዎች መሪ የካሊፎርኒያዋ ዴሞክራት ናንሲ ፔለሲ “ጥንካሬያችን የሚመነጨው ከጤናማ ትምህርትና ከአሜሪካ ሕዝብ የተሣካ ሕይወትም ጭምር ነው” ብለዋል፡፡

የታሰቡት መከላከያውን የማጎልበት፣ ሕግን የማስከበር፣ የወሰን ጥበቃውን የማጠናከር ሥራዎች የሚከናወኑት ወጭዎችን እንደየቅድሚያውና እንደየአስፈላጊነቱ በማሸጋሸግ እንጂ ሃገሪቱ አሁን ባለባት ዕዳ ላይ አንዳችም ተጨማሪ ወጭ ሳያስከትል እንደሆነ የትረምፕ የበጀት ቢሮ ዳይሬክተር መልቨኔ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን ዩናይትድ ስቴትስ የእርዳታ ልገሣ ጉዳይ “በዓለም ዙሪያ የብዙዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል” ሲሉ የሰብዕና ጉዳዮች ተሟጋቾች ድምፆቻቸውን እያሰሙ ነው፡፡

በ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት ላይ የውጭና የውስጥ ምላሾች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

በማደግ ላይ ካሉ ሃገሮች ጋር አሜሪካ የመራራቋ ነገር የሚጎዳው በአመዛኙ
እራሷን አሜሪካን ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ አመራር ጥምረት ባልደረባዋ ሊዝ ሽራየር ለቪኦኤ በስካይፕ ሲናገሩ “ቻይና አለች እኮ፡፡ በልማት ላይ በንቃት በመሠማራት ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ የቻይና መስተጋብር ከሰባት መቶ ከመቶ ተመንድጓል፡፡ እኛ ከአካባቢው ከወጣን እነዚያ ሃገሮች ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሸቀጦችን አይናገዱም፤ አገልግሎቶችን አይለዋወጡም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አንድ የድንጋይ ከሰል አምራች ስለአፍሪካ የሚያውቀው አንዳች ነገር አይኖርም ማለት ነው፡፡ ከምርቱ ተጠቃሚዎች ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆኑት የሚገኙት ደግሞ ከአሜሪካ ውጭ ነው፡፡ በምጣኔ ኃብታችን ላይ የምናውለውን መዋዕለ-ነዋይ ለመደገፍ የሚያስችል ጥሪት ልናገኝ የምንችለው ደግሞ ከነዚያ የሸቀጣ ሸቀጥና የአገልግሎቶች ልውውጦች ነው” ብለዋል፡፡

ሃገሮች በሽታዎችንና ወረርሽኞችን፤ የሽብር ሥጋቶችን፣ የተፈጥሮና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ አደጋዎችን፣ ረሃብና ቸነፈርን ሲዋጉ ከጎናቸው አለመቆምና አለማገዝ ዳፋውና መዘዙ ውሎ አድሮ ይህቺኑ ሃገር - አሜሪካን ወደ ማሳደድ ነው የሚዞረው - ጉዳቱ የሚተርፈው ለራሷ ነው የሚሉ ተቺዎችም በስፋት ይሰማሉ፡፡

ትረምፕ እያደረጉ ያሉት በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት አደርጋለሁ እያሉ ቃል የገቡትንና የተመረጡበትን ሁሉ አንድ በአንድ እራሱን ነው ሲሉ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣናት ይከራከራሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት ላይ የውጭና የውስጥ ምላሾች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG