በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት ረቂቅ ወደ ኮንግረስ ተላከ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “አሜሪካ ትቅደም” በጀታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “አሜሪካ ትቅደም” በጀታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ያቀረቡት በጀት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ወጭና የውጭ እርዳታን የሚቆርጥ፤ ከዚያ በሚገኘው ገንዘብም የመከላከያውን በጀት የሚያሰፋ መሆኑ ታውቋል፡፡

የበጀት ቅነሳው የአባባቢ ጥበቃ ኤጀንሲውንም እንደሚያካትት ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዛሬ ወደ ተወካዮች ምክር ቤቱ ከላኩት የበጀት ጥያቄ ጋር ባያያዙት ማስታወሻ ትልቁ የቅድሚያ ትኩረታቸው የሃገሪቱን ደኅንነት ማስጠበቅ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

“ያለ ደኅንነት ብልፅግና የለም” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

ይህ አዲስ በጀት ለመከላከያ መሥሪያ ቤቱ የ54 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ የሚጠይቅ ሲሆን ለሕክምና ምርምርና ለመጠለያ አልባ የጦር ተመላሾች ተመድበው ከነበሩ ወጭዎች ላይ ተቀናሽ እንዲደረግ የተነደፈ ነው፡፡

ይህ የፕሬዚዳንት ትረምፕ የመጀሪያ በጀት የሚሸፍነው ከፊታችን መስከረም 21/2010 ዓ.ም. /በኢት. የዘ. አቆ/ ከሚጀምረው የበጀት ዓመት አንስቶ ያለውን ጊዜ ነው፡፡

ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱና ከውጭ እርዳታ ላይ እስከ 28 ከመቶ የሚደርስ ወጭ እንደሚቀነስም ተጠቁሟል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት ረቂቅ ወደ ኮንግረስ ተላከ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG