የምስራቅ ወለጋ ዞን ስሬ ወረዳ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት በፈረጀውና እራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ጦር ብለው በሚጠሩ ታጣቂዎች የሚደርስባቸው ጥቃት መጨምሩን፣ ሰዎች መገደላቸውን፣ ንብረት መውደሙንና የተፈናቀሉ ሰዎችም ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ።
በተያያዘ ዜና ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ ሀረር ጃርሶ በሚባል ስፍራ በባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ላይ "ከህብረተሰቡ መካከል የጦር መሳሪያ የታጠቁ የአማራ ተወላጆች ስምንት ሰዎችን ገድለውብናል፤ ንብረታችንንም አቃጥለውብናል" ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የፌደራል መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው "ሸኔ" በማለት መንግስት የሚጠራቸው ታጣቂዎች በኦሮምያ ውስጥ የሚኖሩ የሌሎች የብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግጭቱን የብሔር መልክ ማስያዝ ይፈልጋሉ" ሲሉ ለቪኦኤ ምላሽ ሰጥተዋል።