አዲስ አበባ —
የትግራይ ጠገዴና የአማራ ጠገዴ በሚባሉ አዋሳኝ ወረዳዎች የነበሩ የወሰን ችግሮች፣ መፈታታቸውን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
በጎንደር ከተማ የተካሄደው የአማራና የትግራይ ሕዝቦች ሁለተኛ ዙር የአንድነት ጉባዔ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የቃል አቀባዩ አቶ ንግሱ ጥላሁን እንዳሉት ከዚህ አንፃር የተሰራው ሥራና የተገኘው ውጤት ለጉባዔ ታዳሚዎች ቀርቧል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ