በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብርን ማዳከም ወይስ ምርታማነትን ማሳደግ?


ብርን ማዳከም ወይስ ምርታማነትን ማሳደግ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:53 0:00

ብርን ማዳከም ወይስ ምርታማነትን ማሳደግ?

ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ አከፋፈል ለማስተካከል ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋራ እያደረገቻቸው ባሉ ድርድሮች፣ የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም አንዱ ኢኮኖሚያዊ መፍትሔ ተደርጎ በምክረ ሐሳብ ደረጃ ስለመቅረቡ ይገለጻል፡፡

ምክረ ሐሳቡ ለዓመታት ሲቀርብ እንደቆየ ያወሱት የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ኀይለ መስቀል፣ መንግሥት ግን ሳይስማማበት የቆየ ጉዳይ ስለመኾኑ ይናገራሉ፡፡

ይኹንና ባለፉት አምስት ዓመታት፣ ብሔራዊ ባንክ የወሰዳቸው የብርን የመግዛት አቅም የማዳከም ርምጃዎች፣ ከመፍትሔ ይልቅ ለዋጋ ንረት እና ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዳርገዋል፤ ይላሉ፡፡

ኢትዮጵያ ዘንድሮ ዕዳዋን ሳትከፍል ቀረች - ዘገባ፣ ምላሽና ትንታኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:05 0:00

የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ዶክተር አክሎግ ቢራራም፣ ይህ ዐይነቱ የፖሊሲ ርምጃ በተሞከረባቸው ሀገራት ውጤት እንዳላመጣ ያስረዳሉ፤ በምትኩ በምርት እድገት ላይ አተኩሮ በመሥራት፣ ኢኮኖሚውን ከገጠመው ችግር ለማውጣት እንደሚቻል ያመለክታሉ፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ደግሞ፣ ከብሔራዊ ብዙኀን መገናኛዎች ጋራ በነበራቸው ቃለመጠይቅ፣ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመን ለውጥ ለማድረግ ሐሳብ እንደሌለው መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG