ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ አከፋፈል ለማስተካከል ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋራ እያደረገቻቸው ባሉ ድርድሮች፣ የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም አንዱ ኢኮኖሚያዊ መፍትሔ ተደርጎ በምክረ ሐሳብ ደረጃ ስለመቅረቡ ይገለጻል፡፡ ምክረ ሐሳቡ ለዓመታት ሲቀርብ እንደቆየ ያወሱት የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ኀይለ መስቀል፣ መንግሥት ግን ሳይስማማበት የቆየ ጉዳይ ስለመኾኑ ይናገራሉ፡፡ ይኹንና ባለፉት አምስት ዓመታት፣ ብሔራዊ ባንክ የወሰዳቸው የብርን የመግዛት አቅም የማዳከም ርምጃዎች፣ ከመፍትሔ ይልቅ ለዋጋ ንረት እና ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዳርገዋል፤ ይላሉ፡፡ የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ዶክተር አክሎግ ቢራራም፣ ይህ ዐይነቱ የፖሊሲ ርምጃ በተሞከረባቸው ሀገራት ውጤት እንዳላመጣ ያስረዳሉ፤ በምትኩ በምርት እድገት ላይ አተኩሮ በመሥራት፣ ኢኮኖሚውን ከገጠመው ችግር ለማውጣት እንደሚቻል ያመለክታሉ፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ደግሞ፣ ከብሔራዊ ብዙኀን መገናኛዎች ጋራ በነበራቸው ቃለመጠይቅ፣ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ተመን ለውጥ ለማድረግ ሐሳብ እንደሌለው መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጃንዩወሪ 15, 2025
የትራምፕ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምን ሊመስል ይችላል?
-
ጃንዩወሪ 15, 2025
"በሱስ የተጠቁ ሰዎች ፈጽመው መዳን ይችላሉ" ዶክተር መስከረም አበበ
-
ጃንዩወሪ 14, 2025
ከርዕደ መሬቱ ማዕከል አካባቢ የሸሹት ተፈናቃዮች አኹንም በንዝረቱ ስጋት ላይ ናቸው
-
ጃንዩወሪ 14, 2025
በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ቡና በወቅቱ ለማዕከላዊ ገበያ አለመቅረቡ ተገለጸ
-
ጃንዩወሪ 14, 2025
“እሳቱ ከርቀት እየታየኝ ነው ቤቴን የለቀኩት” - የሳንታ ሞኒካ ከተማ ነዋሪ